ሀገሬ ቲቪ

የስንዴ እና የዘይት ግዢ

የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ ተፈጸመ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ከማስፍን አንጻር የዋጋ ግሽበትን የመቆጣጠርና የገበያ ዋጋን የማረጋጋት ፋይዳ ያለው የ4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴና የ12.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ተገዝቷል የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት እንደተገጸው ባለፉት ጥቅምትና ህዳር ወራት የ4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ግዢ ተከናውኗል ከዚህ ውስጥ ከ1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ስንዴ ወደ ሃገር ውስጥ የገባ ሲሆን ይህም የስንዴ ዋጋ ከፍ እንዳይል የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ታምኖበታል፡፡ የተቀረውም ስንዴ በተቻለ ፍጥነት ተጓጉዞ ወደ ሀገር ውስጥ አንደሚገባም ታወቋል፡፡ በዚሁ ወቅት የ12.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ግዢ ተፈጽሞ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑም ተመልክታቷል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የምግብ ዘይትና ዱቄት ከውጭ በፍራንኮ ቫሉታ ማለትም አስመጪዎች በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገቡ በመደረጉ የሸቀጦች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል አስችሏል ነው የተባለው በመሆኑም በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም 34.2 በመቶ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በህዳር ወር ወደ 33.0 በመቶ ዝቅ ብሏል። የሕዳር 2014 ወርሀዊ የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ጥቅምት 2014 ጋር ሲነጻጸር በ1.8 በመቶ ቀንሷል በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት 1.0 ከመቶ የጨመረ መሆኑን ከገንዘብ ሚንስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል

በሀገሬ ቲቪ
2022-01-04