ሀገሬ ቲቪ

በአፍሪካ ራስ ማጥፋትን የሚከላከል ንቅናቄ ይፋ ተደረገ

የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ ሀገራት ራስ ማጥፋትን የሚከላከል ንቅናቄ ይፋ አደረገ። ይህ ንቅናቄ በአፍሪካ መጀመሩ ከዓለማችን በርካታ ዜጎች ራሳቸውን የሚያጠፉበት አህጉር በመኾኗ ነው ተብሏል።

ንቅናቄው ጥቅምት 10 የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን በሚከበረበት ዕለት ይጀመራል። በአፍሪካ ከ100 ሺ ሰዎች መካከል 11 ያህሉ ራሳቸውን ያጠፋሉ ። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ100,000 ሰዎች መካከል በዘጠኝ ሰዎች ላይ ከሚሞቱት ሰዎች በአማካይ ይበልጣል።

አፍሪካ “በዓለም ላይ ከፍተኛ የራስ ማጥፋት ድርጊት ከሚፈጽሙባቸው አሥር አገሮች ውስጥ የስድስቱ መኖሪያ ናት” ሲል የዐለም ጤና ድርጅት መናገሩን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-10-07