1497ተኛው የነብዩ መሐመድ የመውሊድ በአል በነገው እለት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ይከበራል ፡፡ በአሉን አስመልክቶ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል ፡፡
የምክርቤቱ ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ህዝበ ሙስሊሙም ባሉን ሲያከብር የነብዩን አስተምሮቶች ሊተገብር ይገባል ብለዋል ፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጸሃፊ በበኩላቸው በአሉ ነገ ሲከበር ስለሚከናወኑ ተግባራት ተናግረዋል። በጳውሎስ ፣ ጥቁር አንበሳ ፣ እና በአሚን ሆስፒአል የሚገኙ ህሙማንን የመጠይቅ መርሃ ግብር ይኖራል ተበሏል።
በአሉን ህዘበ ሙሰሊሙ ሲያከብር ከከፋፋይ አጀንዳዎች በመራቅ በአንድነት እንዲያከብረም ያስፈልጋል ተብሏል ፡፡
በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-07
