ሀገሬ ቲቪ

የሁለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

እንደተለመደው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዓመቱን የመንግስትን ጥቅል አቅጣጫ የሚያሳየውን ንግግራቸውን አድርገዋል ።

በዚሁ ንግግራቸው በሀገሪቱ ባለፈው አመት የተገኙ ስኬቶችንና ተግዳሮቶችን አውስተዋል የህዳሴው ግድብ በመልካም አፈጻጻም ላይ ሆኖ ሃይል ማመንጨት መጀምሩ በአርንጎዴ ልማት የታሰበው መሳካቱ በመልካምነት ከተነሱት ይጠቀሳሉ ።

ሆኖም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተከሰተው ጦርነት የአመቱ አበይት ተግዳሮት ሆኖ መቆየቱን አንስተዋል በመሆኑም በ2015 በጀት ዓመት ሰላም የሰፈነባት አገር ለመፍጠር መንግሥት አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ እንደሚደረግ ነው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ያስታወቁት።

መንግሥት መቼም ቢሆን የሰላም በሮችን አይዘጋም ያሉት ፕሬዚዳንቷ፣ አሁንም የሰላም አማራጮችን ሁሉ ክፍት በማድረግ ጥሪውን እንደሚያቀርብ ተናግረዋል።

ጦርነቱ ተቋጭቶ ሰላም እንዲሰፍን በአፍሪካ ኅብረት የተጀመረው ጥረት ውጤት እንዲያመጣ ከሁላችንም ትብብር ይጠበቃል ብለዋል። ይሁን እንጂ ለሰላም ዝግጁ ባልሆኑ ሃይሎች ላይ መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል።

የአገልግሎት አስጣጥን ለማሻሻልም መንግስት ትኩርት ስጥቶ እንደሚሰራ ነው ፕሬዘዳንቷ ገልጸዋል። የኑሮ ውደነትን ለማስተካከል ልምግብ ሸቀጦች አቅርቦት ትኩርት እንድሚስጥና ይማክሮ ሺኮኖሚውን የእማረጋግት ስራ እንድሚሰራም ፕሬዘዳንት ሳህለውርቅ ዘውዴ ተናግረዋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-10