ሀገሬ ቲቪ

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው

ከ560 ሺህ የሚልቁ ተማሪዎች የ12ተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ ስለመሆናቸው የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁት ተማሪዎች በ130 ማዕከላት ነው የብሄራዊ መልቀቂያ ፈተናውን እየወሰዱ ያሉት።

የትምህርት ሚኒስቴር የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ሂደት በሚመለከት መግለጫ የሰጠ ሲሆን በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት "አንፈተንም" በሚል ለቀው መውጣታቸውን ገልጸዋል።

ምክንያቱ እየተጣራ ነው የተባለ ሲሆን በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ መድረሱንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በአደጋው በአንድ ተማሪ ላይ ሞት በሁለት ተማሪዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በአብርሃም በለጠ
2022-10-10