የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሀገራችን የመጀመሪያውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ጀመረ።
ምድብ ችሎቱ ከንግድ እና ኢንቨስትመንት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የንግድ፣ የባንክ፣ የኢንሹራንስ እና የኮንስትራክሽን የፍርድ ክርክሮች ተለይተው የሚስተናገዱበት ነው።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ ምድብ ችሎቱ ስራ መጀመሩ በሀገራችን የኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ለሚነሱ የዳኝነት ጉዳዮች ፈጣን ፍትህ ለመስጠት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
ዘርፎቹ በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ስር ሲታዩ የነበሩ ናቸው። ምድብ ችሎቱ አምስት የንግድ፣ አምስት የባንክና ኢንሹራንስ እንዲሁም አንድ የኮንስትራክሽን ችሎቶችን በመያዝ በ11 ችሎት የተዋቀረ ነው ተብሏል።
በአብርሃም በለጠ
2022-10-10
