የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደሴ ኮምቦልቻ ተቋርጦ የነበረውን በረራ ነገ ሊጀምር ነው፡፡ አየር መንገዱ በጦርነቱ ምክንያት በአማራ ክልል አቋርጦቸው የነበሩ በረራዎችን ትላንት መጀመሩ ይታወሳል፡ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ የልደት በዓልን አስመልክተው ለሚጎዙ ተጓዦች ታኀሳስ 25 በረራ ጀምሯል፡፡ ዛሬ ደግሞ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው ጽሁፍ እንዳስነበበው፤ ለወራት በረራ ተቆርጦበት በቆየው ኮምቦልቻ ዳግም በረራውን በታኅሳስ 27 እጀምራለሁ ብሏል፡፡ ተጎዦች ስልኮቻቸውን በመጠቀም ትኬት መቁረጥ እንደሚችሉ አብስሯል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2022-01-04
