ሀገሬ ቲቪ

የቻድ ወታደራዊ መሪ የስልጣን ቆይታቸውን አራዘሙ

የቻድ ወታደራዊ መሪ ጀነራል ማሃማት ደቢ የሽግግር መንግስቱ ፕሬዝዳንት ነኝ ሲሉ ቃለ መሃላ ገቡ። የስልጣን ቆይታቸውንም በሁለት ዓመት አራዝመዋል ተብሏል። ጀነራሉ የስልጣን ጊዜያቸውን ያራዘሙት ከብሄራዊ ምክክር በኋላ ነው።

ባለፈው ዓመት የጀነራሉ አባት ኢድሪስ ደቢ ለመገደላቸው ተጠያቂ የተደረጉት የተለያዩ ተቃዋሚ ቡድኖች እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የቻድን መጻኢ ፖለቲካ ከሚወስነው ንግግር ራሳቸውን አቅበዋል።

አሜሪካ ሽግግሩን ወታደራዊ አስተዳደሩ የሚያራዝም ከሆነ በሀገሪቱ ላይ ማዕቀብን እጥላለሁ ያለች ሲሆን የአፍሪካ ህብረትም ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያን ለቻድ ሰጥቷል።

በአብርሃም በለጠ
2022-10-10