ሰሜን ኮሪያ የቅርብ ጊዜ የሚሳኤል ማስወንጨፏን በደቡብ ኮሪያ ላይ የኒውክሌር ጥቃት ሙከራ ነው አለች።
የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰፊው እንደዘገበው ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች የኒውክሌር መሳሪያዎችን መሸከም የሚችሉ ናቸው ተብሏል።
በቅርቡ ሀገሪቱ ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ላደረጉት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሰባት ሚሳኤሎችን በማስወንጨፍ ምላሽ ሰጥታለች።
የደቡብ ኮሪያን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ማውደም የሚችል ለአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ማስጠንቀቂያ የሚሆን የተሳካ ሙከራ አድርገናል ሲሉም ዘግበዋል።
በአምስት ዓመታት ውስጥ ሃገሪቱ የመጀመሪያው የኒውክሌር መሳሪያዎች ሙከራዋን ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች ስለመሆኑ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።
በአብርሃም በለጠ
2022-10-10
