ሀገሬ ቲቪ

ለየት ያለው የፋሽን ትርዒት

ይህች የምንኖርባትን ዓለም ሰዎች ዘመናትን ሁሉ በራሳቸው ልክ ሲሰሯት እና ሲያስተካክሏት ዛሬ ላይ የደረሰች ናት።

ታዲያ ከሚታወቀው ሰውነት በትንሹ የተለወጡ ነገሮችን ከተፈጥሮ አለመቁጠር እና ማኮሰስ ዛሬም ድረስ ያለ የዓለማችን ህመም ነው።

ሰዎች በቆዳ ቀለማቸው፣ በፊት ቅርፃቸው፣ በአነጋገራቸው፣ በፆታቸው እና በቁመታቸው ሳቢያ በርካታ ፈተናዎች ይደርሱባችዋል።

ይህ ሁሉ ፈተናዎች አሉባት በምትባለዋ ዓለም ውስጥ ደግሞ ሌሎች ቀና ሀሳቦች የሞሉባቸውም ሰዎች አልታጡም። ታዲያ እኛም እንዲህ ያለው በጎ ሀሳብ ይባልን የሚያሰኝ ተግባርን ሰማን እና ልናጋራችሁ ወደድን።

ቻሚያህ ዴዊ የተባለችዋ ዲዛይነር በተፈጥሮ አጭር ሆነው ለተወለዱ ወይንም ድንክ ተብለው ለሚጠሩ ሰዎች የሚሆኑ አልባሳትን ታዘጋጃለች።

በባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ዓመት የጀመረችው በጎ ሀሳብ አሁን ፍሬን እያፈራ ይገኛል። ሁኔታው በዘረ መል አልያም በህክምና ሊከሰት የምኒችል ስለመሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ።

እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች በዓለም ላይ የተገለሉ እና የተገፉፉ ናቸው የምትለው ዴዊ እነሱን ማገ እና ማየት ይገባል ትላለች።

ታዲያ አሁን በኒው ዮርክ የፋሽን መድረክ ላይ ለእነዚሁ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሆኑ የሴቶች አልባሳትን ይዛም ብቅ ብላለች። በመድረኩም ላይ እነኚሁ ድንክ ወይዛዝርት በተዘጋጁላቸው አልባሳት ደምቀውም አምሽተዋል።

በጣም ጥቂት አማራጮች፣ የዋጋቸው መወደድ እና በሚፈለገው መጠን አለማግኘት ችግሮች የፋሽን ኢንዱስትሪው ላይ እንደሚስተዋሉ ይነገራል።

በተለይ የፋሽን ኢንዱስትሪው ለእነርሱ የሚሆኑ አልባሳትን በየእድሜ ደረጃቸው በበቂው መተን ማዘጋጀት አለመቻሉ አስገርሞኛልም ትላለች።

በሳምሶን ገድሉ
2022-10-11