ሀገሬ ቲቪ

ናይጄሪያ ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ዜጎቹን መደጎም ጀመረች

የአፍሪካ ትልቁ ምጣኔን ሀብት የምትሸፍነው ናይጄሪያ በምግብ ዋጋ ውድነት እየተፈተነች ነው። የምግብ ዋጋ ግሽበት 23.12 በመቶ ኾኗል።

በዚህም የዋና ከተማዋ ሌጎስ የምግብ ባንክ የምግብ ዋጋ አልቀመስ ላላቸው ዜጎቹ ድጋፍ ማድረግ ጀምሯል።

ይህ በጎ ፈቃደኛ ድርጅት ድጋፍ የሚደረግላቸው ዜጎች ምግብ የመግዛት አቅማቸው ደካማ የኾነ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እንደኾኑ አፍሪካ ኒውስ አስነብቧል።

17 ሚሊዮን የናይጄሪያ ህፃናት ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተጋለጡ ናቸው። በሀገሪቱ ያለው የዋጋ ግሽበት በዚሁ ከቀጠለ በ2022 መጨረሻ ተጨማሪ 1ሚሊዮን ዜጎች ለድህነት ይጋለጣሉ ይላል የዓለም ባንክ ትንበያ።

በሙሉጌታ በላይ
2022-10-11