ሀገሬ ቲቪ

በጋምቤላ ክልል በክረምቱ ወራት በርካታ የቀንድ ከብቶች ሞተዋል

በጋምቤላ ክልል ላሬ፣ጅካዎ፣ማኩዌይና ዋንትዋ ወረዳዎች በክረምቱ ወራት በዘነበው ዝናብና ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በርካታ የእንስሳት ሀብት ለሞትና ለግጦሽ ችግር መጋለጣቸው ተሰማ።

በክልሉ ከፍተኛ የእንሰሳት ሀብት የሚገኝበት አከባቢ እንደኾነና በዚያው ልክ በተፈጥሯዊ አደጋም ይሁን በሌላ ችግር እንስሳቱ ለሞት እንደሚዳረጉ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በማኀበራዊ ገጹ አስታውቋል።

ምን ያህል የቀንድ ከብቶች በጎርፍ አደጋው እንደሞቱ ግን አልተገለጸም።በተያያዘም በተጠቀሱት ወረዳዎች ከ400 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የዳልጋ ከብቶች የጎሮርሳ በሽታ ክትባት እየተሰጠ ነው ተብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-10-11