ሀገሬ ቲቪ

በቱኒዚያ የምግብ ዋጋ ንረት የዜጎቿን ሕይወት እየፈተነ ነው

የምግብ ዋጋ መጨመር እና የምግብ እጥረት የ ሰሜን አፍሪካዋን ሃገር ቱኒዚያን እየፈተነ ይገኛል ።

የሩሲያ ዩከሬን ጦርነት ለደሃዋ አፍሪካ ወትሮም በልቶ ለማያድረው ህዝቧ ሌላ ራስ ምታት መሆኑን እያሳየ ይገኛል። ከቅርብ ሳምንታት ጀምሮ በቱኒዚያ የምግብ ዋጋ መናር እና እና የመሰረታዊ የሽቀጦች ዋጋ ከ አረብ አብዮት በኋላ በሰፊው መጠን መጨመሩ ተሰምቷል።

እንደ ሰኳር፣ የአትክልት ዘይት ፣ ሩዝ እና የታሸጉ መጠቶች ከሱፐር ማርኬቶች እና ከ ግሮሰሪዎች መጥፋታቸው በሃገሪቱ ታይቷል ።

የሃገሪቱ ህዝቦችም መሰረታዊ የእለት ፍጆታዎችን ለሟሟላት በመንግስት ከሚደጎሙ ተቋማት ረጅም ሰልፍ እየተጠባበቁ ይገኛሉ ።በአሁን ወቅት የሃገሪቱ ዜጎች መሰረታዊ የምግብ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት እንደማይችሉ ነው የተዘገበው ። ይህ እጥረትም በዚሁ ከቀጠለ ነገሩን ወደ ተቃውሞ እንዳይወሰደው ተሰግቷል ።

መንግስት በበኩሉ ለገበያው መናር የጥቁር ገብያው እና የዩክሬን ሩሲያ ጦርነተን እንደ ምክንያት ያነሳሉ ። እንደ መጣኔ ሃብት ባለ ሞያዎች ከሆነ የመንግስት የበጀት ቀውስ ፣ከውጭ አበዳሪ ተቋማት በድር አለመገኝት እና መንግስት ከአበዳሪ ተቋምት ጋር የሚያደርገው ድርድር ፍሬያማ አልመሆን ለተፈጠረው ቀውሰ ዋንኛ ምክያት ነው ይላሉ።

ከመንግስት የሚሰጠውን የምግብ እርዳታ የሚወስድ ዜጋ በመብዛቱ የሚፈጠረው መጨናነቅ ከፖሊስ ጋር ግጭጥ እንዲፈጠር ምክያት እየሆን ነው።

በ2010 ስራ በማጣቱ ሳቢያ እራሱን በአደባባይ እንዳቃጠለው ቡአዚዝ ሁሉ ከዚሁ የኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ በዋና ከተማዋ ቱኒስ በአትክልት ሻጭነት የሚተዳደር አንድ ወጣት እራሱን ማጥፋቱን ተገልጿል። የዚህ ወጣት ህልፈት የ2010ን ተቃወሞ እንዳይደግመወ ተሰግቷል ።

የቱኒዚያ የንግድ ሚንሰትር የሞሊድ በአል ከመድረሱ በፊት የስኳር እጥረቱን ለመቅረፍ ከህንድ 20ሺ ቶን እንዳስገቡ ቢገልጽም ነዋሪዎች ከበአሉ ቀደም ባለው ምሽት ላይ ሱፐር ማርኬቶች በረጅም ሰልፎች ተሞልተው ታይተዋል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-11