ሀገሬ ቲቪ

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኤርትራ መግባት

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ዩ ትላንት ማምሻውን ኤርትራ መግባታቸው ተነገረ፡፡ ሚንስትሩ ለሁለት ቀን የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ኤርትራ መግባታቸውን የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል የኤርትራ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ኡስማን ሳለህ እና ሌሎች መንግሥት ባለሥልጣናት ለቻይናው ልዑክ አቀባበል አድርገውላቸው፡፡ አስመራ የገቡት የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ዩ በቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከከውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ኡስማን ሳለህ ጋር እንደሚወያዩ የሀገሪቱ ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል አስታውቀዋል በምን ጉዳይ ውይይት እንደሚያደርጉ ግን ቃል አቀባዩ አልገለጹም፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2022-01-05