የአለም በየዐለቱ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ታሰተናግዳለች። የፈጠራዎች ሁሉ ምክንያቱ ደግም ችግር ነው ። በሰዎች የዐለት ተእለት እንቀሰቃሴዎች ትራንሰፖርት ዋንኛ ጉዳይ ነው ።
ግን በየትኛውምሃገር እንከን አያጣውም አንድ አንዱ ጋር እጥረት ሌላው ጋር ደግሞ በብዛቱ ሳቢያ የሚመጣ የመንገድ መጨናነቅ ከወደ ዱባይ የተሰማው የቻይናውያን የቴክኖሎጂ ፈጠራ የሆነው ግኝት ይህን በመኪና ብዛት አልያም በመንገድ ጥበት የሚፈጠርን መጨናነቅን የፈታል ተብሎለታል።
ይህ በዱባይ ሰማይ ላይ የተሳካ ሙከራውን ያደርገው በራሪው መኪና ሁለት ሰዎችን የመያዝ ሽቅም አለው ። ኤክስ ሁለት የሚል ስያሜ የተሰጣት ይች መኪና ካሻት ቦታ ማረፏ እንደሊሎቹ በራሪ አካልት ሰፊ ቦታ አልመፈልጓ መንገድ ሲመች ደግሞ ልክ እንደ ሽየሩ ሁል ብምድሩም ብር ማለት መቻሏ አስወድዷታል።
በራሪዋ ተሽከርካሪ በግራ እና በቀኝ በተገጠሙላት 8 ተሽከርካሪ ከንፎች አየሩን ለመቅዘፍ ትጠቀማለች ነው የተባለው ። የቻይና ኤሌክትሮኒክስ ተሽከርካሪ አምራች የሆነው ዥፒንግ ኢንክ ለወደፊት ለሚሰሩ የበራሪ መኪኖች መሰረት የጣለች ናት በልዋታል።
መኪናዋም በሙከራ ጊዜዋ ያለማቋረጥ 90 ደቂቃ ያክል አየሩን ስትቀዝፍ ቆይታለች። የመኪናዋ የፍጥነት ወሰን በሰዐት 80 ኪሎ ሜትርን መሆኑም ነው የተገልጸው ።
በኤሌትሪክ የምትሰራ ከበካይ ጋዝ ልቅትም ነጻ መሆኗ አለም ለያዘችው የካርቦን ልቀትን ወደ ዘሮ የማውረድ መንገድ መኪናዋን ድንቅ ፈጠራ ያሰኛታል።
መኪናዋን ያመረትው ድርጅት እንዳለው በቀጣይ ለአለም አቀፍ ገበያ በስፋት ለማቅረብ እየሰራ ነው። ዱባይ የቴክኖሎጂ ከተማ መሆኗ ለበራሪዋ መኪና መሞከሪይነት እንዳስመረጣት የኩባንያው ሃላፊዎች ተናግረዋል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-12
