ሀገሬ ቲቪ

የህዝበ ውሳኔ ጥር 29 ይካሄዳል

ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል በሚገኙ 6 ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሄደው ሕዝበ ውሣኔ የትግበራ አፈጻጸም ዝርዝር ዕቅድ አወጣ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሠሌዳ መሰረት ጥር 29 2015 የህዝበ ውሳኔው የሚካሄድበት ቀን ነው። አጠቃላይ ውጤት የሚገለጽበት ቀን ደግሞ የካቲት 8 ይሆናል ብሏል። የመራጮች መዝግባም ታህሳስ 6 እስከ 25 ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይከናወናል ብሏል።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-12