በዘንድሮ የጃይቴክስ 2022 ዱባይ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ፤ ኢትዮጲያም ለመጀመሪያ ጊዜ የግብርና ፤ የአይ/ሲ/ቲ እና የዲጅታል ቴከኖሎጂዎችን መሰረት ባደረጉ አስር የፈጠራ ስራዎች እተሳተፈች ነው።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር አመቻችነት የግሉን ዘርፍ በማስተባበር ነው እነዚህ ተቋማት በኤክስፖው ማሳተፍ የተቻለው።
ስታርታአፖቹ ያቀረቧቸው የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ከጎብኚዎቹ አበረታች ምላሽ እያያገኙ እንደሆነም ተገልጿል። የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሚኒስቴር ደኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ በኤክስፖው መሳተፍ የኢትዮጲያ ስታርትአፖች በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ዘልቀው እንደገቡ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በኤክክፖው ከ170 በላይ አገራት የመጡ ታላላቅ ዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ስታርትአፖች እየተሳተፉ ይገናኛሉ።
በብሩክ ያሬድ
2022-10-12
