የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞችን ከማጓጓዝ ባለፈ የካርጎ ወይም የጭነት አገልግሎት በመስጠት በዓለም ኾነ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል ይሁን እንጂ፤ ከዚህ አገልግሎቱ ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ቅሬታ የሚያነሱ ደንበኞች አሉ።
በተለይም ንብረትን ቶሎ መረከብ አለመቻል እና ሌሎች ችግሮች ከዚሁ ጋር የሚነሱ ናቸው።ይህን ችግር የበፊት ነው አሁን ላይ ብዙ ለውጦች አሉ ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
አየር መንገዱ በአገልግሎት ዘርፉ ከደንበኞች የሚነሱበትን ቅሬታዎች ቅድሚያ ሰጥቶ መፍታቱን እንደሚቀጥልበትም አቶ ጣሰው ተናግረዋል። በዚህ ጥረቱም በመስከረም ወር በሰጣቸው አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን አገኝቷል። እነዚ ሽልማቶች አሁንም ቢኾን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን የበለጠ ከፍ ለማድረግ የቤት ሥራ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
በካናዳ ሞንትሪያል ከተማ በተካሔደው የአለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት 41ኛ ጉባኤ ኢትዮጵያ ካለችበት ምድብ ሁለተኛውን ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት የምክር ቤቱ አባል ለመሆን ችላለች፡፡
ከዚህ ባለፈ አየር መንገዱ ምርጥ የአለማችን 100 አየር መንገዶች ዝርዝር ውስጥም 26ኛ ደረጃን ይዟል። በ 2023 ይህን ደረጃ ለማሻሻል ዕቅድ ስለመያዙ ሰምተናል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለረጅም ዓመት ሲገለገልበት የቆየውን የመንገደኞች አውሮፕላን ሙሉ በሙሉ ወደ እቃ ጫኝነት በመቀየር ጥቅምት02/2015ዓ.ም ይፋ አድርጓል ይህ ሥራው በአፍሪካ የመጀመሪያ እንደኾነ ተጠቁሟል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-10-13
