ሀገሬ ቲቪ

38 ሆቴሎችን ያሰናዳችው ላልይበላ

በላልይበላ የሚገኙ 38 ሆቴሎች ለገና በዓል እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ተባለ፡፡ የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በላልይበላ ለሚያከብሩ እንግዶች በሆቴሎች ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡ የቢሮው ኃላፊ መሪጌታ መልካሙ ዓለሙ በላሊበላ ከተማ 42 ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድን አራቱን ሙሉ በሙሉ ስድስቱን በከፊል ማውደሙን ተናግረዋል በተመሳሳይ በዚሁ ቡድን በላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ሆቴሎች እና መሠረተ ልማቶች ላይ ውድመትና ዝርፊያ ማድረሱ ይታወሳል፡፡ ቡድን ከተማዋ ከተወገደ በኋላ በከፊል የወደሙትን በመጠገን 38 ሆቴሎች ለበዓሉ ዝግጁ ተደርገዋል፡፡ ህውሀት በላሊበላ ባደረሰው ውድመት አሁን ላይ በከተማ የሚታየውን የኤሌክትሪክ እና የውሀ ችግር ለመቅረፍ የተደረገው ስራ ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን መርጌታ መልካሙ ዓለሙ ተናግረዋል፡፡ በላሊበላ ከተማ የሆቴል ኢንዱስትሪ ከሦስት ሺሕ በላይ ሠራተኞችን ያቀፉ ሲሆን ሆቴሎቹ ዳግም ወደ ስራ መግባታቸው በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች መነቃቃትን የሚፈጥር ይሆናል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2022-01-05