የዛምቢያ የስደተኞች ባለሥልጣን 43 ኢትዮጵያዊ ስደተኞችን ማባረሩን ገለጸ።
ስደተኞቹ በሕገወጥ መንገድ ወደ ዛምቢያ መግባታቸውን ተከትሎ በፍርድ ቤት የተወሰነውን የቅጣት ገንዝብ ከከፈሉ በኋላ ነው ከዛምቢያ እንዲወጡ የተወሰነው።
20 የሚኾኑት ወንድ ስደተኞች ከ 15 እስከ 35 በሚሆን የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
ከመስከረም 8 / 2020 ጀምሮ እስካሁኑ በተወሰደ እርምጃ 344 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በሕገወጥ መንገድ ወደ ዛምቢያ እንደገቡ በመረጋገጡ ከሀገሪቱ እንዲወጡ መደረጋቸውን ሲጂቲኤን አስነብቧል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-10-13
