ሀገሬ ቲቪ

ሕንድ በጋምቢያ ለሞቱት ህጻናት የተጠረጠሩ ሽሮፖች እንዳይመረቱ አገደች

የአለም ጤና ድርጅት በጋምቢያ ለሞቱት ህጻናት ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ያላቸውን ፈሳሽ መድሀኒቶች የሕንድ የጤና ባለስልጣን እንዳይመረቱ ትዕዛዝ አስተላለፈ።

የሕንድ የጤና ተቆጣጣሪዎች የሳል ሽሮፖቹ አምራች የሆነው ማይድን የተሰኘው ድርጅት በምርትና በሙከራ ሂደት ሕጎችንና ደንቦችን ጥሶ አጊንቼዋለሁ ብለዋል።

የህጻናቱን ህልፈት በተመለከተም በአሁኑ ወቅት በሕንድ እና በጋምቢያ ምርመራዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት በጋንቢያ ለሞቱት 70 ህጻናት ምክንያቱ የወሰዱት የሳል ሽሮፕ ሊሆን ይችላል ማለቱ ይታወሳል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-10-13