ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ የመታወቂያ ዕድሳት ሊጀመር ነው

በአዲስ አበባ ከተማ ታግዶ የነበረው የመታወቂያ ዕድሳት በያዝነው ወር መጨረሻ እንደሚጀምር ተገለጸ። ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ናቸው።

በመታወቂያ አሰጣጥ እና ዕድሳት ላይ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት የመታወቂያ ዕድሳት በከተማዋ ታግዶ እንደነበር የገለጹት አቶ ጥራቱ ባልተገባ ድርጊት ላይ ተሳታፊ የነበሩ ባለሙያዎች እና አመራሮች ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል።

ከመታወቂያ ጋር በተያያዘ ያልተገባ ተግባር ክትትል በክፍለ ከተሞች፣ በተለይም ችግሩ በጎላባቸው 37 ወረዳዎች 90 አመራሮች እና ባለሙያዎች ተጠያቂ ስለመደረጋቸው ዋና ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-10-14