ሀገሬ ቲቪ

ቡርኪና ፋሶ ለብሔራዊ ምክክር ልትቀመጥ ነው

በቡርኪናፋሶ በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን የያዘውን ወታደራዊ ኃይል በመፈንቅለ መንግሥት ያወረደው አዲሱ ወታደራዊ ኃይል የብሔርዊ ውይይት ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ።

ሀገሪቱ ከውይይቱ በኋላ የሽግግር ግዜ ፕሬዚዳንቷን ትመርጣለችም ተብሏል። በውይይቱ ከሀገሪቱ መከላከያ፣ ከፖሊስ፣ ከባህል እና ከሀይማኖት ተቋማት፣ ከሲቪል ማህበረሰብ፣ ከንግድ ህብረቶች እና ፓርቶዎች እንዲሁም በጂሀዲስት ቡድኖች ጥቃት ከደረሰብቸው እና ከተፈናቀሉ ዜጎች የተወከሉ አካታት ይታደሙበታልም ነው የተባለው።

የሁለተኛ ግዜ መፈንቅለ መንግስት አድራጊው የካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ደጋፊዎች ካፒቴኑ የሽግግር ግዜው ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ፍላጎት አላቸው ተብሏል።ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ኝ ሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ሆኖ የመምራት ፍላጎት የላቸውም መባሉን አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-10-14