ሀገሬ ቲቪ

የአዲስ አበባ ምክር ቤት ያጸደቃቸው ሹመቶች

የአዲስ አበባ ምክር ቤት በሁለተኛ ዓመት የስራ ዘመን በአንደኛ መደበኛ ጉባኤው የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ።

የከተማዋ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ የነበሩት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ኾነዋል ፣ በሳቸው ቦታ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተሹመዋል። አቶ ምትኩ አስማረ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኾነዋል።

ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ ፣ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፣ አቶ ጀማል ረዲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን በምክርቤቱ ቀርበው ፀድቀዋል።

በተያያዘም ምክር ቤቱ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩን የወ/ሮ ሃቢባ ኡመር ያለመከሰስ መብታቸውን አንስቷል። ወ/ሮ ሃቢባ፣ በክፍለ ከተማው አርሶ አደር እና የአርሶ አደር ልጅ ያልሆኑ ሰዎችን የመሬት ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ፣ ያለአግባብ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ እንዲሁም በህገ ወጥ መንገድ ይዞታ ማረጋገጫ በመስጠት ተጠርጥረዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-10-14