
በናይጄሪያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከ 600 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ ። ናይጄሪያ በአስር ዓመታት ውስጥ አይታው በማታውቀው በዚህ አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ200ሺ በላይ ቤቶች እንዲሁም ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ወድመዋል ተብሏል።
የጎርፍ አደጋው በናይጄሪያ ከሚገኙ 36 ግዛቶች 27ቱን አዳርሷል። የናይጄሪያ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የጎርፍ አደጋው እስከ ህዳር ወር መጨረሻ ሊቀጥል ይችላል ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-10-17