ሀገሬ ቲቪ

የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተደረገ

የሰላም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ሶስቱ ተቋማት የተፈራረሙት የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን የሚመለከት ነው። የመግባቢያ ስምምነቱ ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ ያግዛል ተብሎለታል።

የሰላም ሚኒስቴር ዲኤታ ታየ ደንደአ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ ፍስሃ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

ይሄው ስምምነት ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን በትብብር መስራት የሚያስችል ነው ተብሏል።

በአብርሃም በለጠ
2022-10-17