ሀገሬ ቲቪ

‘’የሱዳን መንግስት ኢትዮጵያን በሚጎዳ ማንኛውም ተግባር ላይ ተባባሪ አይሆንም’’ የሱዳን የመረጃ ኤጀንሲ ኃላፊ

የሱዳን የመረጃ ኤጀንሲ ኃላፊ ሜ/ጄነራል መሐመድ አሊ አህመድ የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ እና መንግስት በሚጎዱ ማናቸውም ተግባር ላይ ተባባሪ አይሆንም ሲሉ ገለጹ።

በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደረጉት የሱዳን የመረጃ ኤጀንሲ ኃላፊው በጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር መክረዋል። ሜ/ጄነራል መሀመድ አሊ በሁለቱ ሀገራት ድንበር መካከል በተደጋጋሚ የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ሜጀር ጀኔራል ደምሰው አመኑ በሀገራቱ መካከል የተፈጠሩት ችግሮች ለመፍታት ብሎም ችግሮች እንዳይፈጠሩ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸውላቸዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-10-17