ሀገሬ ቲቪ

የአፍሪካ ኅብረት በድጋሜ የሰላም ጥሪ አቀረበ

በሰሜን ኢትዮጵያ በሚካሄደው ጦርነት ተሳታፊ ወገኖች ባስቸኳይና ያለ ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙ የአፍሪካ ኅብረት ዳግም ጥሪ አቀረበ።

የህብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት አዲስ ባወጡት መግለጫ ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንደገና እንዲጀምር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በደቡብ አፍሪካ በሚካሄድ አፍሪካ ኅብረት-መራሽ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ቀደም ሲል የገለጹትን ስምምነት በድጋሚ እንዲያረጋግጡም አሳስበዋል። ሙሳ ፋኪ የሰላም ንግግሩ ወደፊት የሚካሄድበትን ቀን ግን አልገለጡም።

የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት ለሚካሄደው የሰላም ውይይት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል። ሕወሃትም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሙሳ ፋኪ ማህማትን የድጋሜ ጥሪ መቀበሉን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-17