ሀገሬ ቲቪ

የነዳጅ ዋጋን የቀነሰችው ደቡብ አፍሪካ

ደቡብ አፍሪካ በነዳጅ ዋጋ ላይ ማስተካካያ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡ በሳይንሳዊ ስያሜው 93 በተሰኘው ነዳጅ ዓይነት የ71 ሳንቲም ቅናሽ የተደረገ ሲሆን በተመሳሳይ 93 በተሰኘው ነዳጅ ዓይነት ደግሞ የ68 ሳንቲም ቅናሽ መደረጉን የሀገሪቱ ማዕከላዊ ኢነርጂ ፈንድ አስታውቋል የኬሮሲን ዋጋ በሊትር 71 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑን ፊን 24 የተሰኘው የሀገሪቱ የዜና ምንጭ ጽፏል የሀገሪቱ የነዳጅ ዋጋ የሚወሰነው በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ እና በዶላር ራንድ የምንዛሬ ዋጋ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ አመት በሀገሪቱ የነዳጅ ዋጋ ከ14 ራንድ ወደ 20 ራንድ ከፍ ብሎ ነበር የነደጅ ዘይት ዋጋ መጨመር ደግሞ ምክንያቱ ነበር፡፡ አሁን ላይ ግን ቅናሽ መደረጉ የደቡብ አፍሪካ አሽከርካሪዎችን እፎይታ እንዲሰማቸው አድርጓል ተብሏል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2022-01-05