የኢትዮጲያን ፖለቲካዊ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከሃገራዊ ምክክር ወጭ ሌላ አማራጭ የለም ብሎ እንደሚያምን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ ።
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበርሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በበኩሉ ሁሉም ዜጎች በሃገራዊ ምክክሩ እንዲስታፉ ተገቢወን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል።
ሀገራዊ ምክክር እና ውይይት ተቀባይነት እያገኘ የመጣ የግጭት መፍቻ ሁነኛ አማራጭ ነው ፡፡ ዘላቂ ሰላም እና የሰከነ የፖለቲካ መድረክን እውን ለማድረግ ይረዳል በሚል ።
ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ ዝግጅቷን ከጀመረች ከረም ብላለች ፡ እስከ አሁን አሰፈላጊ የተባሉ ተግባራትም ሲከወኑ ቆይተዋል ።
በሀገራዊ ምክክሩ ዜጎች እና ሀገሪቱ የሚገኙ ፖለቲካ ፓርቲዮችም የራስቸው የሆነ የድርሻን እንዲወጡ ይጠበቃል ። እስክ አሁን ባለው የሃገርዊ ምክክር የሰራ ሂደትን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተሳትፎው ምን ይመስላል ስንል ጠይቀናል።
የሃገርዊ ምክክር ሁሉን አቀፍ መሆንን የሚሻ ትልቅ ጉዳይ እንደመሆኑ የዜጎች ተሳታፊን በበዙ ይፈጋል። ዜጎች በሃገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ያላቸውን ተስታፎ እና ግንዛቤ ከማሳደግ አንጻርም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት ምን እየሰራ ይሆን።
ሀገራዊ ምክክሩ በአንድ ተቋም ብቻ የሚከወን ሰራ ባለመሆኑ በሂደቱ ላይ ዜጎች በንቃት እንዲሳትፉም ተጠይቋል ።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-17
