ሀገሬ ቲቪ

የ12ተኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ተጀመረ

የ12ተኛ ክፍል የሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች ያለምንም ችግር በሰላም መጀመሩ ተገለጸ። ይህንን ያሉት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።

ሚኒስትሩ አክለውም ከመጀመሪያው ዙር ተምረን ብዙ ነገሮችን ስላስተካከልን የዚህ ፈተና በተጀመረበት መልኩ እንደሚጠናቀቅ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

በቀጣይ በፈተና ስርዓቱ ያሉ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ቀርፈን ወደ አዲስ ምእራፍ እገባለንም ብለዋል። የ2ኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

በአብርሃም በለጠ
2022-10-18