ሀገሬ ቲቪ

“ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ለኢኮኖሚው ፈተና ነው” ብሄራዊ ባንክ

ብሄራዊ ባንክ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን አሰመልከቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የህገ ወጥ የገንዝብ ዘውውር ለሃገራዊ ኢኮኖሚው ፈትና ነው ብሏል ። ህገወጥ ዝውውሩን ለመቆጣጠር የተስሩ ስራዎች አበረታች ቢሆኑም አሁንም ትኩረትም ይሻሉ ተብሏል ።

ብሄራዊ ባንክ በቂ የወርቅ ወደተቋሙ በበቂ መጠን እየቀረበ አይለም አለ ፡፡ ባንኩ የህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው ይህን ያለው ።

የኮንትሮባንድ ንግዱን ለመቆጣጠር ሰፊ ተግባራት ቢከናወኑም በተወሰነ መንገድ ክፍተት አሳይቷል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የገንዘብ መጠን ማያዣ ፖሊሲ ወደ ሁለት አመት እየተጠጋው ነው ተብሏል ፡፡ ዜጎች ከባንክ ውጪ ያለን የብር መጠን በጥሬ መቶሺ ብር መያዝ የሚችሉ ሲሆን ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ተቋማት ደግሞ 200ሺ መያዝ እንደሚችሉ ይታወቃል ፡፡

ብሄራዊ ባንክም ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከውጭ ሀገር ለሚገባ የወጭ ምንዛሬ ስለሚኖሩ እንቅስቃሴ ተከታዩን ብለዋል ፡፡

ባንኩ በቅርቡ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩን ለሚጠቁሙ ዜጎች ወረታውን እከፍላለሁ ማለቱን ተከትሎ ስለአጠቃላይ መመሪያ ማብራሪ ሰጥቷል ፡፡ዜጎች ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩን በሚጠቁሙበት ወቅት ስጋት እንዳይገባቸው ምስጥራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን ባንኩ አሳውቋል፡፡

በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-19