
ሱማሊያ መንግስት አልባነቷ አክትሞ አቅሙ የደርጅ ባይሆንም ምንግስት መስርታ እንደሃገር ለመቀጠል ጥረት እያደረገች ነው አሁንም በአጥፍቶ ጠፊ ያልሸባብ ጥቃር መታመሷ ባይቆምም አሁን ደግሞ ተፈጥሮም ፊቷን አዙራባታለች ።
የሱማሊያ አርሶአደሮች ለአራት ተከታታይ አመታት በቂ ዝናብ አላገኙም ድርቁምም በርትቶባቸዋል አሁንም ለአምስተኛ ጊዜ ድርቁ እንደሚቀጥL ነው የአየር ትንበያዎች ያመለከቱት ።
ይሄ ጉዳይ ለሱማሊያ በንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባታል ። በድርቁ ሳቢያ ከ50 ዓመታት ወዲህ የመጀመርያው አስከፊው ርሃብ ከፊቷ መደቀኑን ነው የተባበሩት መንግስታት ያስታወቀው ።
እስካሁን ባለ መረጃ 7 ነጥB 8 ሚሊየን የሚጠጋ ማለትም የሃገሪቱ ህዝብ ቁጥር ግማሽ የሚሆነው ለርሃብ ተጋልጧል ።
ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 213ሺዎቹ ባስቸኳይ የምግብ እርድታ ካልተደረገላቸው ለሞት ይዳረጋሉ ብሏል የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ኤጀንሲ።
በሱማሊያ የተከስተው ርሃብ ሞት እንዳያስከትል ለማደረግ ደጋፍ ያማደርግበት 2 ቢልየን ዶላር ያስፈልግኛል ያለው ኤጀንሲው የድረሱልኝ ጥሪ ለለጋሾች አቅርቧል። የኤጀንሲው ኃላፊ ማርቲን ግሪ ይሄንንው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሱማሊያ እንደአውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በ2011 አግጥሟት በንበረው ድርቅ 260 ሺ ዜጎቿን አጥታለች ይህኛው ደግሞ ከዚያም የከፋ በመሆኑ አለም አቀፍ ርብርብ ካልተደረገ የሚደርሰው ጉዳት እጅግ የከፋ ይሆናል ተብሏል።
በተለይ ለህጻናቱ ቶሎ እንድረስላቸው የተባበሩት መንግስታት የድጋፍ ጥሪ ነው። በሩሲያና በዩክሬን ጦረነት ሳቢያ የምግብ አቅርቦት እንደአለምም እጥረት ያለ መሆኑ ግን የእርዳታ አቅርቦቱን እንዳያስተጓጉለው ተሰግቷል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-10-19