ሀገሬ ቲቪ

የአሜሪካ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ እንድትመለስ ግፊት ማድረግ አለባቸው ተባለ

የአሜሪካ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ካለቀረጥ ምርቶቿን ወደ አሜሪካ ገበያ ማስገባት ወደ ሚያስችላት አጎዋ እንድትመለስ ግፊት እንዲያደርጉ ተጠየቀ ።

ጥያቄው የቀረበው በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ከ50 በላይ ከሚሆኑ የአሜሪካ ባለሀብቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው ።

በውይይቱ ኢትዮጵያ ከአጉዋ እንድትወጣ የተወሰነው ውሳኔ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ከመጉዳቱ ባለፈ በርካታ ዜጎች ስራቸውን እንዲያጡ አድርጓል ተብሏል ።

በመሆኑም የአሜሪካ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ ተጠቃሚነቷ እንድትመለስ ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን አምባሳደር ስለሺ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-10-19