ከወዳደቁ ቁርጥራጭ የቆዳ ተረፈ ምርቶች የማጣበቂያ ኮላ መሥሪያ ጄላቲን በማምረትና ወደ ውጪ በመላክ ከ 4 መቶ ሺሕ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በማኀበራዊ ገጹ አስታውቋል።
ይህ የውጪ ምንዛሬ የተገኘው ጂያንዚን ዛንግ ክረስት ኤንድ ፊኒሽድ፤ የክረስትና ያለቀለት ቆዳ አምራች በኾነው ድርጅት ነው ተብሏል። ድርጅቱ ሥራ ከጀመረ ሁለት ወራትን አስቆጥሯል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-10-19
