
ማሊ ፈረንሳይ የአየር ክልሌን በመጣስ ላማጽያን ድጋፍ እያደረገች ነው ስትል ከሰሰች።
የማሊ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አብዱላሂ ዲኦፕ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክርቤት እንዳሉት ፈረንሳይ በሰሜናዊ ማሊ ለሚንቀሳቀሱ አማጽያን በአይሮፕላን የታገዘ የመሳርያ ድጋፍ እያደረገች ነው።
ይህ የሃገር ሉአላዊነትን መጣስ በመሆኑ ምክርቤቱ አንድ ሊላት ይገባል ብለዋል።
በፈረንሳይ የተባበሩት መንግስታት አንባሳደር ኒኮላስ ሬቨሬ ግን ውንጀላውን አስተባብለዋል ። እኛ በማሊ የምናደርገው ጣልቃ ገብነት በግልጽና ዜጎችን በሚጠቅም ጉዳይ ላይ እንጂ እንዲህ ያለው ተግባር ላይ አይደለም ብለዋል። ይህ ተራ ስም ማጥፋት ነውም ብለዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-10-19