ሀገሬ ቲቪ

ገጣሚዋ ሮቦት ለእንግሊዝ ፓርላማ ማብራሪያ ሰጠች

መቼም ቴክኖሎጂ በየጊዜው እያስገረመን ነው የሚገኘው። በተለይ የሮቦት ቴክኖሎጂ በፍጥነት ለውጥ እያመጣ ነው። ሰውን ከማገዝ አልፎ አሁን አሁን ሰውን ለመተካት እየተንደረደሩ ነው።

አለም አቀፍ ዜግነት የተሰጣትና የእኛም ሀገር ልጆች በአፈጣጠሯ ተሳትፎ ካደረጉላት ሶፍያ ከተሰኘችው ሮቦት ሌላ በጣም ለሰው የቀረበች ሮቦት በእንግሊዛውያን ተፈብርካለች ።

አይዳ የተሰኘቸው ሮቦት ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠን ኪነ ጥበብ እኔም መከወን እችላለሁ እያለች ነው ። ለኪነጥበብ የምታደርገውን አስተዋጻኦ በተመለከተም በእንግሊዝ ፓርላማ የኮሚዩኒኬሽን እና ዲጂታል ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፊት ቀርባ ለተነሳላት ጥያቄ ምላሽ ሰጥታለች ።

እንደተነገረው ከሆነ አይዳ ስዕል መሳል ግጥም መግጠም ትችላለች እነዚህ ማሰብን የሚጠይቁት ተግባራት በአግባቡ መከወኗን እንዲሁም እንደሰዎች ሁሉ በተጠየቀችው ጉዳይ ላይ ተገቢውን ማብራርያ መስጠቷ አጃኢብ አሰኝቷል።

አይዳም ሰውን ለመተካት ከጫፍ የደረሰች የመጀመርያዋ ሮቦት የሚል ስያሜ አሰጥቷታል።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-19