መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ከሚባሉት ወስጥ አንዱ ሰኳር መሆኑ አጠያያቂ አይደለም። ታዲያ ከ ቅርብ ቀናት ጀምሮ እየናረ የመጣው የስኳር ዋጋ የሸማችሁን የህብረተስብ ክፍል ከ ኑሮ ወድነቱ ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የኑሮ ጫና ወስጥ እንደከተታቸው ነዋሪዎች ገለጹ ።
የህብረተሰቡን ፍጆታ በበቂ ሁኔታ ለመሙላት መንግስት የስኳር ፋብሪካዎችን ለማስፋፋት እየሰራ ቢሆንም አሁንም የህብረተስቡን የስኳር ፈላጎት ማርካት አልተቻለም።ለመሆኑ ከሰሞኑ የታየው የስኳር እጥረት ምክንያት ምን ዪሆን ሰንል ላንሰንላችው ጥያቄ ።
“በክረምቱ ምክያት ለፋብሪካዎች ምርት በበቂ ሁኔታ እይቀረበ ባልመሆኑ እንደሆነ እና አንዳንድ ፋብሪካዎች በጥገና ላይ መሆናቸው ነው ብለዋል” የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር።
በስኳር እጥረቱ ሳቢያ ስኳርን ለህብረተሰቡ ማድረስ ያቆሙ የሸማች ማህበራት እንዳሉ ሁሉ በአንዳንድ የሸማች ማህበራት ለህብረተሰቡ የሚደርሰውን የሰኳርመጠን በመቀነስ ስኳር እየሰጡ እንዳሉ ነዋሪዎች ገልፅዋል ፡፡
ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ የተቀነሰው የስኳር መጠን ኮታ በዛው የሚቀጠል ነው በሚል ስጋታቸውን ይገልፃሉ ።
ከሰሞኑ የታየውን የሰኳር እጥረት በዘላቂነት ለመፍታትም እየተወስዱ ያሉ እርመጃዎች ምን ምንድናቸው?ስንል ላንሰናው ጥያቄ መስሪያ ቤቱ ተከትዩን ምላሽ ሰጥቶልናል።
“በ አሁን ወቅት ከ 2 ሚልዮን ሰኳር በላይ ወደ ሃገር በመግባት ላይ ይገኛል በተጨማሪ የፋብሪካዎቹ ጥገና ሲጠናቀቅ አሁን የትከስተው የስኳር እጥረት እና መወደድ ሙሉ በሙሉ ይስተካከላል” በለዋል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-20
