ሀገሬ ቲቪ

የዓለም ህዝብ ቁጥር ዕድገት

አለማችን ያልፉትን ሁለት አመታት በኮቪድ ብቻ 6.5 ሚሊየን ዜጎች አጥታለች ይህ እንግዲህ በጦረነት በድንገተኛ አደጋና በሌሎች በሽታዎች የሚሞተወን ሳይጨምር ነው።

ለነገሩ የተባበሩት መንግስታት በዚህ አመት ጥቅል የሞት ቁጥር 67 ሚሊየን እንደሚደርስ ተንብዩል። በዚህ ሁነታ ውስጥ ነው እንግዲህ የአለማችን ህዝብ በምጪው ታህሳስ 8 ቢሊየን እንደሚደርስ የተባበሩት መንግስታት የስነ ህዝብ ፈንድ ትንበያ የሚያመለክተው።

በዚህ ትንብያ መሰረት ህንድ አንድ ቢሊየን 429 ሚሊየን ዜጎች ያሏት ቀዳሚ ሀገር ትሆናለች ። ይህም ለመጀመርያጊዜ ከቻይና የበላይ እንድትሆን ያደርጋታል። ቻይናም በ2023 ይህዝብ ቁጥሯ 1ቢሊየን 426 ሚሊየን ይደርሳል ።አሜሪካ ኢንዶኔዥያ ፓኪስታንም ቁጥራቸውከ340 ሚሊየን እስከ 240 ሚሊየን የሚደርስ ህዝብ ይኖራቸዋል።

ይህ ባለፉት 10 ዓመታት የተመዘገበ የውልደት ምጣኔ ከ 1 በመቶ በታች እንደሆነም ተገልጿል። ይህ እድገትም ቢሆን በሰባት ሀገራት ላይ የበልጥ ከፍ ብሎ ይታያል። ኢትዮጵያ ናይጄኢያ ዲሞክራቲክ ኮንጎና ታንዛኒያ ከፈትኛ የህዝብ ቁጥር እድገት ያለባቸው ሃገራት ተብለው ተጠቅሰዋል። 61 ሃገራት ደግሞ የመወለድ ምጣኔ ቀንሶባቸዋል ነው የተባለው።

የተባበሩት መንግስታት ዋን ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቁጥሩን 8 ቢሊየን መደረሱ መልካም ነው ነገርግን ለምድራችን በማሰብ ና ምቹ የኑሮ ከባቢ ለመፍጠር ቁርጠኝነቱ ሊያድግ ይገባል ብለዋል።

በማይመች አለም የሚፈተር የሰው ልጅ እንዳይኖር ጦረነት ማቆም ላረንጓዴ ልማት ትኩረት መስጠት ድህነት ቀነሳ ላይ መሰራት ይገባልም ይላሉ ጉተሬዝ።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-20