ሀገሬ ቲቪ

የንብረት ታክስ መጣል የሚያመጣው ተጽዕኖ ይኖር ይኾን?

መንግሥት ንብረት ላይ የሚጣል አዲስ ታክስ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል። ይህ የግብር ዓይነት ግለሰቦች አሊያም ተቋማት በሚኖራቸው ቤት፣ ሕንጻዎች፣ መሬት፣ ተሽከርካሪዎች፣ በአክሲዮን እና ሌሎች መሰል የተመረጡ ሐብቶችን መሠረት አድርጎ የሚጣል ነው።

ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ይህ ታክስ እስካሁን ተፈጻሚ ኾኖ አያውቅም። የሀገሪቱ ሕገመንግሥት ስለታክስ አሰባሰብ እና ክፍፍል በዝርዝር ያሰቀመጣቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ንብረት ታክስን ጨምሮ ከታክሱ የሚሰበሰበው ገቢ ለክልሎች ይሁን ለፌደራል መንግሥት የሚለውም አልሰፈረም ይህ በመኾኑ ታክሱ ለማን ይገባል የሚለው አሻሚ ጉዳይ ኾኗል።

በአ.አ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምሕር እና ባለሙያ የኾኑት ረ/ፕሮፌሰር አስቻለው አሻግሬ በንብረት ታክስ ላይ በርካታ ጥናቶችን ሰርተዋል።

የንብረት ታክስ ገቢ ለማን ይገባል ለሚለው በሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ታክሱ ንብረቱ አሊያም ያለበት ክልል ነው የሚሰበስበው ብለዋናል።

ከዚህ ባለፈ ይህን የንብረት ታክስ ለመንግሥት ተጨማሪ ገቢ በማስገኘት የመሠረተ ልማት ግንባታ በከተማሞች እንዲስፋፋ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር የምጣኔሀብት ባለሙያው ዶ/ር አረጋ ሹመቴ ተናግረዋል ከዚህ ባሻገር ግን በተጠናከረ መዋቅር ካልተመራ ብዝበዛ እና ሌላ የኑሮ ውድነት መንስ ዓኤ ሊኾን እንደሚችል ገልጸዋል።

የንብረት ታክስ ሲጣል የተጠቀሱት አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይከሰት ግብሩ ከመጣሉ በፊት ሊሰሩ የሚገባቸው ጥልቅ ጥናቶች እና ቅድመኹኔታዎች እንዳሉ ነው ምሁራኑ የተናገሩት።

በሙሉጌታ በላይ
2022-10-20