ሀገሬ ቲቪ

ገቢያቸው ትሪሊየን ዶላር የደረሰው የዓለማችን ቱጃሮች

5 መቶ የአለማችን ቱጃሮች በፈረንጆቹ 2021 ያገኙት ገቢ ቢሊየን ዶላርን ተሸግሮ ትሪሊየነር ደርሷል ተባለ። ከቀናት በፊት ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት አምስት መቶ የዓለማችን ቱጃሮች አጠቃላይ ገቢ ወደትሪሊየን ዶላር አድጓል። እንደብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ የአምስት መቶው ባለሃብቶች ድምር ሃብት ስምንት ነጥብ አራት ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም በምጣኔ ሐብታቸው ልዕለ-ሃያል ናቸው ከሚባሉት ከቻይና እና አሜሪካ ውጭ ካሉ የትኛውም ሃገር ጂዲፒ በላይ እንደማለት ማለት ነው። የዓለማችን ቁጥር አንድ ቱጃር ለመሆን የበቃው ኤለን መስክ ባላፉት 12 ወራት ብቻ 1መቶ18 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝቷል። የእነዚህ ቱጃሮች አመታዊ ገቢ ትሪሊየን ዶላር በደረሰበት ተመሳሳይ ዓመት 150 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በድህነት እጅ ስለመውደቃቸው የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያሳያል።

በሀገሬ ቲቪ
2022-01-05