ሀገሬ ቲቪ

ሩስያ የተባበሩት መንግስታት የኢራንን ድሮኖችን እንዳይመረመር አስጠነቀቀች

ሩስያ በዩክሬን ጦርነት ጥቅም ላይ ውለዋል ስለተባሉት የኢራን ድሮኖች የተባበሩት መንግስታት ምርመራ እንዳያደርግ አስጠነቀቀች።

የተባበሩት መንግስታት የመካከለኛው ምስራቅ የጦር መሳሪያ ገደብን ይጥሳል በሚል የኢራንን ድሮኖች እመረምራለሁ ብሏል። አሜሪካ ፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ የጸጥታው ምክር ቤት ስለድሮኖቹ በዝግ እንዲመክር ጥሪ አቅርበዋል።

ድሮኖቹ ሲቪል ዜጎች ላይ እና መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ውድመት ያደርሳሉ ያሉ ቢሆንም ሩስያ እና ኢራን ግን የተባበሩት መንግስታት ይሄንን የመመርመር ስልጣን የለውም ብለዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-10-20