
የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጅላይና የሀገሪቱን ውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ማባረራቸው ተሰማ ።
የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ የተባረሩት ሩሲያን ለማውገዝ በተጠራው የተባበሩት መንግስታት ጉባኤ ላይ ዩክሬንን ደግፈው ድምጽ በመስጠታቸው ነው ።
ሩሲያ የዩክሬንን አራት ግዛቶች መጠቅለሏን ተከትሎ በተጠራው ጉባኤ 143 ሀገራት ሩሲያን ማውገዛቸው ይታወሳል ።
የድጋፍ ድምጹን ከሰጡት መካከልም የማዳጋስካር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር መገኘታቸው የሀገሪቱን መሪ በእጅጉ አበሳጭቷል ።
ውጪ ጉዳይ ሚኒስተሩ ድምጹን በሰጡ ማግስት በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ማንንም ሳያማክሩ እንዳደረጉት የተነገረ ሲሆን አሁን ደግሞ መባረራቸውን አፍሪካን ኒውስ አስነብቧል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-10-20