ሀገሬ ቲቪ

በማላዊ 25 ኢትዮጵያዊ ስደተኞች አሉበት የተባለ የጅምላ መቃብር ተገኘ

በማላዊ 25 ኢትዮጵያዊ ስደተኞች አሉበት የተባለ የጅምላ መቃብር መገኘቱ ተገለጸ ።

አስከሬኑ የተገኘው በማላዊ ሰሜናዊ ግዛት ምዚምባ በሚባል ደን ውስጥ እንደሆነ የሀገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል ።

ከአስከሬኖቹ መካከል ከ25 እስከ 40 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወንዶች አሉበት የተባለ ሲሆን የሞታቸው መንስኤ እየተጣራ ነው ተብሏል።

በማላዊ 2022 ከገባ 221 ስደተኞች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 186ቱ ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-10-20