በአፍሪካ ኅብረት አመቻችነት የሚደረገው የመንግስትና የሕወሃት የሰላም ንግግር ለመጭው ሰኞ ጥቅምት 14 መጠራቱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሚንስትር ሬድዋን ሁሴን በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡
መንግስት የሰላም ውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆኑንም ሚንስትሩ አረጋግጠዋል። የህወሃት ቡድን ሰኞ ተጠርቷል ሰለተባለው የሰላም ውይይት እስካሁን ምንም ባይልም ከዚህ ቀደም የቀረበውን ጥሪ መቀበሉ ይታወሳል።
የሰላም ንግግሩ ለመጪው ሰኞ የተቀጠረው ከዚህ ቀደም የአፍሪካ ህብረት ከሁለት ሳምንት በፊት ንግግሩን ለማስጀመር ያስተላለፈው ቀጠሮ ከተሰረዘ በኋላ ነው፡፡
በብሩክ ያሬድ
2022-10-20
