ሀገሬ ቲቪ

የላልይበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለማደስና ለማልማት ፈረንሳይ ድጋፍ አደርገች

የላልይበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለማደስና ለማልማት እንዲቻል በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መንግስት መካከል የ260 ሜሊዮን ብር የዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የገንዘብ ሚንስትር ዲኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰውና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ልማት ኤጀሲ ዳይሬክተር ሚስዝ ቫሌሪዬ ቴሂኦ ፈርመውታል፡፡

የእርዳታ ስምምነቱ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከአራት ዓመት በፊት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳነት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በተወያዩበት ወቅት ሁለቱ ሀገራት በቅርስ ጥበቃ ረገድ ትብብር ለማድረግ በተስማሙት መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ፕሮጀክት አካል ነው ተብሏል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-21