ሀገሬ ቲቪ

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ

በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረው 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች ሲሰጥ በነበረው ፈተና ከ900ሺህ በላይ ተማሪዎች በ130 የፈተና ማዕከላት ተፈትነዋል።

ፈተናው በመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሂደት ካጋጠሙ ችግሮች ውጪ በታቀደው መሰረት በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።ተፈታኞችም ከዛሬ ጀምሮ ወደ የአካባቢያቸው መመለስ መጀመራቸውን አስታውቋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-21