ሀገሬ ቲቪ

የአሳማ ልብ ለሰው

የአሳማ ልብ የተቀየረለት ግልሰብ ወደ ዕለት ኑሮው ተመልሷል መባሉን ሰማን፡፡ ከዚህ ቀደም የአሳማ ኩላሊት ለሰው ልጅ የመተካት ሙከራ ስለመደረጉ ሰምተን አብረን ተገርመን ነበር፡፡ ጭራሹኑም አሁን የአሳማ ልብ የተቀየረለት ግልሰብ ወደ ዕለት ኑሮው ተመልሷል መባሉን ተዘግቧል፡፡ አዲሱ የህክምና ውጤት በጨለማ ውስጥ የፈነጠቀ አዲስ የተስፋ ብርሃን ነው ተብሎለታል፡፡ ዴቪድ ቤኔት የተባለው አሜሪካዊ የልብ ህመሙ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው የመጨረሻው አማራጭ የደከመው ልቡን በሌላ ልብ መተካት ነበር፡፡ ታዲያ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የሜሪላንድ የህክምና ዩኒቨርሲቲ የተሻለ አማራጭ አለኝ ብሏል፡፡ የዩንቨርስቲው ቤኔትን ከሞት ይታደግ ዘንድ የአሳማ ልብ ንቅለ ተከላን በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል፡፡ የ57 ዓመቱ ጎልማሳ ወደ ቀዶጥገና ክፍሉ ከመግባቱ በፊት እንደተናገረው እኔ መሞት አልፈልግም ለዚህ ይህንን መርጫለው ብሏል፡፡ የአሳማ ልብ ከሰው ልብ ጋር በእጅጉ የሚመሳሰል በመሆኑ የተሻለ አማራጭ ነው ብለዋል የህክምና ቡድኑ አባላት፡፡ ከዚህ ቀደም ኩላሊት፣ ጉበት እና ሳንባ ከአሳማ የሰውነት ክፍል ውስጥ ውጥተው በሰው ሰውነት ውስጥ ያገለግሉ ዘንድ ሙከራዎች እየተደረጉባቸው ይገኛሉ፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2022-01-11