ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ማህበር ስራዎቼን በአግባቡ እንዳላከናውን የዋጋ ንረት እና የምርት እጥረት እየፈተነኝ ነው አለ

የሰሜኑ ጦርነት ፤ የውጪ ምንዛሬ እጥረት እንዲሁም ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ሀገራችንን ክፉኛ እየፈተናት ይገኛል ።

ታዲያ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት የኢኮኖሚ አለመረጋጋት በርካታ ዘርፎችን እየጎዳ ይገኛል ። ከዚህም ውስጥ ለሀገሪቱ ዕድገት ከፍ ያለ ድርሻ ያለው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አንዱ ነው።

ዘርፉ ስራዎችን በአግባቡ ሰርቶ ለማጠናቀቅ እንዲሁም አዳዲስ ስራዎችን ለመጀመር የግንባታ ግብአቶች የዋጋ ንረት እንዲሁም ሊቀየሩ የሚገባቸው አስተዳደራዊ ውሳኔዎች በእጅጉ እየፈተኑት እንዳለ የኢትዮጵትያ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ግርማ ሀብተ ማሪያም ነግረውናል።

ኢንጂነሩ በዋጋ በኩል የሚታዩትን ከፍተኛ ጭማሬዎች ተቋቁሞ ለመግዛት ቢፈለግም ምርቶች በበቂ ሁኔታ ገበያ ላይ አለመኖራቸው ሌኛው ፈተና ነው ብለዋል ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-10-21