የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት በፌደራል መንግስት እና በህወሃት ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውይይት ውጤታማ እንደሚሆን ተስፋውን ገለጸ። ምክር ቤቱ ይህንን ያለው ስለጉዳዩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ በተያዘው የሰላም ውይይቱ የፌደራል መንግስትም ሆነ የህወሃት ቡድን ተወካዮቻቸውን ልከዋል።
የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው ልኡካን ለሰላም ውይይቱ መላካቸውን ገልጾ መከላከያ በትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን መቀጠሉን በተጨማሪም የሰላም ውይይቱን ጦርነቱን በሰላም ለመቋጨት ዕድል አድርጎ እንደሚመለከተው አስታውቋል።
በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ከህብረተሰቡ በመነጋገር ሕዝባዊ አስተዳደር የሚቋቋምበትንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚጀምሩበትን መንገድ እየተመቻቸ ስለመሆኑም ገልጿል።
በአብርሃም በለጠ
2022-10-24
